ትምህርት እና ጊዜ የማይነጣጠሉ የውጤት ቁልፎች

22-11-2025 18:45pm

ትምህርት የረጅም ጊዜ ሂደት ነው፤ ጊዜ ደግሞ የዚህ ሂደት ነዳጅ ነው። ጊዜያችንን በግባቡ በተጠቀምን ቁጥር፣ የትምህርት ውጤታችን ብቻ ሳይሆን ደስተኝነታችንም ይጨምራል። ዛሬ፣ በተለይ ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት ወደ ውጤት እንደሚቀየር እንመለከታለን ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ሲባል ምን ማለት ነው? ብዙዎቻችን ጊዜን መጠቀም ማለት ቀኑን ሙሉ በመጽሐፍ ተከቦ መዋል ብቻ ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን፣ ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ማለት በከባድ መስራት ሳይሆን በብልሃት መስራት ነው። በተብራራ ሁኔታ የሚከተሉትን ያካትታል፡- 1. እቅድ : ነገ የምንሰራውን ስራ ዛሬ ማቀድ ይገባናል፡፡ 2. ቅድሚያ የሚሰጠውን መለየት ፦ ሁሉንም ነገር በአንዴ ማድረግ አይቻልም። አስቸኳይ እና ጠቃሚ የሆኑ የትምህርት ስራዎችን ለይቶ ማስቀደም ይገባል። 3. ትኩረትን የሚሰርቁ ነገሮችን ማስወገድ ፡ የጥናት ሰዓት ሲደርስ ስልክን ማራቅ፣ ቴሌቪዥን መዝጋት እና ሙሉ ትኩረትን ወደ ትምህርት ማድረግ። 4. የእረፍት ጊዜን ማካተት: አእምሯችን መረጃን ለማስቀመጥ እረፍት ያስፈልገዋል። ያለ እረፍት ለረጅም ሰዓት ማንበብ የጊዜ ብክነት እንጂ ትርፍ የለውም፡፡ 1. ለመምህራን፡ አርአያነትዎ ይናገራል! መምህራን የጊዜን ዋጋ በተግባር የሚያሳዩ መሪዎች ናቸው። • የክፍል ሰዓት አጠቃቀም፡ በተመደበው ክፍለ ጊዜ በሰዓቱ ገብቶ በሰዓቱ መውጣት ለተማሪዎች ትልቁ የዲሲፕሊን ትምህርት ነው። • እቅድ ማውጣት፡ የትምህርት ይዘቱን ካለን ጊዜ ጋር አብቃቅቶ ማስተማር ተማሪዎች እንዳይጨናነቁ ይረዳል። • ምክር፡ መምህራን ለተማሪዎቸቸው የትምህርት ይዘትን ብቻ ሳይሆን፣ ያንን ይዘት እንዴት ጊዜ ሰጥተው ማጥናት እንዳለባቸውም ይምከሯቸው። 2. ተማሪዎች፡ ጊዜ የናንተ ትልቁ ሀብት ነው! ተማሪዎች ሆይ፣ ጊዜ ተመልሶ የማይመጣ ብቸኛው ሀብታችሁ ነው። • ፕሮግራም ይኑራችሁ፡ በዘፈቀደ አታጥኑ። የትኛው ትምህርት መቼ እንደሚጠና በእቅድ ለዩ። • የነገ እሰረዋለሁ የሚባል ልምድን አስወግዱ፡ የዛሬን ስራ ለነገ ማሳደር የጭንቀት ሁሉ መጀመሪያ ነው። • የትኩረት ጊዜ: ያለትኩረት ረጅም ጊዜ ከማንበብ ይበልጥ በተመስጦ አነስ ላለ ጊዜ ማንበብ ይሻላል። 3. ለወላጆች፡ ድጋፍ እና ክትትል! ልጆች የጊዜ አጠቃቀምን የሚማሩት ከቤት ነው። • በጋራ ማቀድ: ከትምህርት መልስ የሚኖራቸውን የመመገቢያ፣ የጥናት እና የመጫወቻ ሰዓት በጋራ በመሆን ወስኑ። • ስክሪን እና ጊዜ: በሶሻል ሚዲያ እና በጌም ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ይገድቡ። • አርአያ ይሁኑ: እርስዎ እራስዎ ጊዜዎን በአግባቡ ሲጠቀሙ ሲያዩ ልጆችም ይከተላሉ። (የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

ወደ ዋናው ገጽ ለመመለስ